የ hub4africa የቅድሞው ፕሮጀክት ምዕራፍ
የፕሮጀክቱ ጅምር እና የመጀመሪያው ምዕራፍ የገንዘብ ድጋፍ ውጤቶች
የ"hub4africa" ፕሮጀክት በአፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ለማስተዋወቅ ብዙ ቋንቋዎችን ያካተተ መድረክን ለመፍጠር በማለም የተጀመረ ነው ። ቡድኑ ከተመረጠበት እና ፅንሰ-ሀሳቡ ከዳበረ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተጠናከረ የስራ ዕቅድ ምእራፍ የቴክኒክ እና የንድፍ መስፈርቶቹን ከአፍሪካ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በቅርበት በመተባበር በግልጽ አስቅምጧል።
መድረኩ እ.ኤ.አ. ከፈብሩዋሪ እስከ ኤፕሪል 2022 ተዘጋጀ፡ ሶስት ቋንቋዎች ያካተተ ድህረ ገጽ (በጀርመንኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ)፣ የሙድል ትምህርት መድረክ በኤስኤምኤስ ምዝገባ እና የመነሻ ይዘቶችን መፍጠር እና መተርጎም።
ይህ የመድረክ ተምሳሌት በኪጋሊ፣ ሩዋንዳ በሚገኘው በአፍሪካ ኢ-Learning ቀርቦ በይፋ እ.ኤ.አ. ማይ 2022 ተጀመረ። ከዚያ በኋላ ደገሞ ይህ እ.ኤ.አ. ከጅን እስከ ዲሴምበር 2022 የሚቆይ የመድረኩ የማስፋፊያ ምዕራፍ ተከትሏል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የመድረኩ ይዘት እና አቅርቦቶች ተዘርግተዋል። እንዲሁ በዓመቱ መገባደጃ ላይ፣ የመጀመሪያ የሥልጠና ፕሮግራሞችን የያዘው መድረክ በፖርቹጋልኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም የማህበራዊ ሚዲያ ግብይት ፅንሰ-ሀሳብን በመፍጠረ እና መድረኩ በፌስቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ሊንክድድ ላይ በራሱ ቻናሎች እንዲተዋወቅ ተደርጓል።
እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ እስከ ጅን 2023 በነበረው የመጨረሻው ምዕራፉ ላይ ያተኮረወ መድረኩን ማመቻቸት እና በተጨማሪ ማስፋፋት ላይ ነበር። በመጨረሻው የገንዘብ ድጋፍ ዘመኑ መድረኩ የአረብኛን ቋንቋን በማካተት ፣ የመጀመሪያ የስልጠና ኮርሶችን በአረብኛ ቋንቋ ሰጥቷል። መድረኩን በብቃት መጠቀም፣ እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን ለሌሎች ለማድረስ እንዲችሉ አሰልጣኞች ሰልጥነዋል። ስለዚህም "hub4africa" በዘለቄታ ከዒላማው ቡድኖች ጋር ተቀናጅቶ በቋሚነት ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል።
በተቀነባበረ እና በታለመ አተገባበር፣ በአፍሪካ ውስጥ ለዲጂታል ትምህርት ትልቅ አስተዋፅዖ የሚያደርግ እና አለም አቀፍ ትስስርን የሚያበረታታ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ እና ሁለገብ መድረክ ተፈጥሯል።
ምዕራፍ 2 መድረኩን ማስቀጠል እና ማስፋፋት፡-
በሁለተኛው የገንዘብ ድጋፍ ምዕራፍ፣ hub4africa በይዘትም ሆነ በቋንቋ ስልታዊ በሆነ መንገድ ይበልጥ እንዲዳብር እና እንዲስፋፋ ተደርጓል። አንዱ ትልቅ ምዕራፍ የአማርኛ ቋንቋ ወደዚህ መድረክ መጨመሩ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ካሉት ቡድኖቹ ፍላጎት ጋር በተሻለ መልኩ እንዲጣጣም አስችሎታል። እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 31 ቀን 2024 በፕሮጀክቱ መጨረሻ ፣ አቅርቦቱ በስድስት ቋንቋዎች ከ 490 በላይ የመማሪያ ሞጁሎችን አድጓል።
በተጨማሪም በአፍሪካ ውስጥ የትምህርት እና የስራ መስክን ምስረታን ገጽታ በዘላቂነት በማጠናከር፣ የመምህራን የብቃት መለኪያ እና የኣዲስ የስራ መስክ ፈጣሪዎች ስልጠና የበለጠ በዘላቂነት ተስፋፍተዋል።
በዚህ ደረጃ፣ በመድረኩ ላይ ያሉት የንቁ ተሳታፊዎች እና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ27,000 በላይ ጨምሯል። ስለዚህም hub4africa በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ በሙያ አማካሪነት እራሱን እንደ ቋሚ መድረክ ያቋቋመ እና በሙያ ስልጠና እና በአለም አቀፍ ትስስር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው።
ሌላው ፈጠራ ደግሞ "በጀርመን መኖር እና መስራት" የሚለው የአዲሱ ፕሮግራም ዘርፍ ነው። ይህ ፕሮግራም በተለይ በሙያ ሰለጥነው ወደ ጀርመን ለመሰደድ ለሚፈልጉ ግለሰብዎች የተዘጋጀ ዘርፍ ሲሆን ዘርፉ አስፍላጊ ሞጁሎችን አካትቷል.