የሀይሮጅን ማሽን ቴክኒሻን
ይህ ሙያ የሚያጠነጥነው የሃይድሮጂን ማሽንን በተመለከተ፣ የመጨረሻው መገጣጠም፤ መትከል ፤ ወደሰራ ማስገባት ፤ አገልግሎት መስጠት እና መጠገን ዙሪያ ነው።
ስራዎን ያሳዩ በያጅ !
ማንቃት ያስፈልጋል
ይህን ቪዲዮ በመጫን የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ማየት ይችላሉ፤ከነቃ በኋላ ዳታ ወደ ዩቲዩብ እንደሚተላለፍ ልንገልጽልዎ እንወዳለን። በገጹ ላይ በማንኛውም ጊዜ ይህንን ማንቂያ ማጥፋት ይችላሉ፡፡ ግላዊነት.
የሀይሮጅን ማሽን ቴክኒሻን ስራ ምንድነው ?
የአረንጓዴ ሃይድሮጂን ኢንዱስትሪ በዓለም ዙሪያ እያደገ ነው። የአለም ሀገራት በተነሳሽነት በ2050 አለም አቀፋዊ የአየር ንብረት ብከላን ሙሉ በሙሉ ዜሮ ማድረስን፣ እውን ለማድረግ ሲጥሩ ሃይድሮጂን እንደ ንፁህ የሃይል ምንጭ አማራጭ በመሆን ጥቅም ላይ እየዋለ መምጣቱን ጨምሯል። እንደ ሃይድሮጂን ማሽን ቴክኒሻን ፤ የሃይድሮጂን ማምረቻ ፋብሪካ ወስጥ ያሉ ማሽኖች እንዴት እንደሚሠሩ እና እንዴት መንከባከብ እንዳልቦት ይማራሉ። የሃይድሮጂን ማሽን ቴክኒሻኖች ዋናውን የመገጣጠም፤ የመትከል፤ ወደሰራ የማስገባት ፤ አገልግሎት የመስጠት፣ የመንከባከብ ፤ የመጠገን እንዲሁም የሃይድሮጂን ጣቢያዎችን የመጠበቅ ሃላፊነት ስለሚወስዱ፣ የሃይድሮጂን ፋብሪካ ስራዎችን በተመለከተ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- ስለ ሜካትሮኒክ ስርዓቶች ጥሩ እውቀት (ለምሳሌ ፦ ተቀጣጣይ ጋዞች እና ከፍተኛ የግፊቶች ያሉበት ቦታ ላይ ሲሰሩ)
- የኃላፊነት ስሜት
- በሥራ ወቅት ያሉ የደህንነት ሂደቶችን እና የአደጋ ግምገማን መረዳት እና መተግበር
ለሀይሮጅን ማሽን ቴክኒሻን የሚሆኑ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ፣ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣በሙያወ አቅጣጫን ለማስያዝ ይረዳል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያው የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀታቸውን ለማዳበር ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ይህ ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና በሙያው አዳዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው።