ብረት መቁረጥ
የብረት ቆራጭ ስራ ምንድነው?
የብረት መቁረጫ ማሽን ላይ ይሠራሉ እንዲሁም የብረት ምርቶችን ያመርታሉ። የሚሰሩባቸው ምርቶች በቅድሚያ በደንበኛው የታዘዙ ናቸው። ስለዚህ በዝርዝሩ መሰረት መመረት አለባቸው። አብረዎት የሚሰሩት ማሽኖች በኮምፒውተር ቁጥጥር ስር ናቸው። የበረት ቆራጭ ማሽን ኦፕሬተር ተግባራት ማሽኖቹን ፕሮግራም ማድረግ ፣ ኦፕሬቲንግ እና ቁጥጥርን ያጠቃልላል ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- ትክክለኛ ስራ (ለአብዛኛዎቹ ምርቶች በጣም ተጠንቅቆ መስራት ያስፈልጋል)
- ቴክኒካዊ ችሎታዎች (ከማሽኖቹ ጋር ለመስራት ፣ ቴክኒካዊ ግንዛቤ ሊኖርዎት ይገባል)
- በት እዛዙ መሰረት ትክክለኛ ስራ (የደንበኛ ዝርዝሮች መከበር አለባቸው)
- የእቅዶች ትርጓሜ (ምርቱን ለማምረት የምርቱን እቅድ መረዳት አለቦት)
- ትዕግስት
ሊወዷችው የሚችሉ ሌሎች ዘርፎች
የማሽን ንፅህና ፣ ማሞቂያ እና አየር ማቀዝቀዣ
ይህ ሙያ ዘርፍ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶችን መተግበር እና የአየር ማቀዝቀዣዎችን መትከል እና መስራት ነው።
የማሽን ባለሞያ
ይህ የሙያ ዘርፍ ትክክለኛ የብረት ቅርጻ ቅርጾችን በመሥራት ላይ ያተኩራል።
የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ባለሙያ
ይህ የሙያ ዘርፍ የኤሌክትሪክ ስራዎች ላይ ያተኩራል።
ሜካትሮኒክስ ቴክኒሻን
ይህ የስራ ዘርፍ የሜካትሮኒክስ ሲስትም መስራት ያካትታል።