በያጅ
የበያጅ ስራ ምንድነው ?
እንደ በያጅ፣ በተለያዩ የኢንዱስትሪ መስኮች (ከስካፎልዲንግ እስከ አውሮፕላን ቴክኖሎጂ) የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን (በተለይም ብረቶች፣ ግን እንደ ፖሊመሮች ያሉ ፕላስቲኮች) ይበይዳሉ። የስራ ክፍሎች እና በረቶች ሙቀትን ወይም ግፊትን በመጠቀም አንድ ላይ ተጣምረው አንድ ክፍል ይመሰርታሉ። በስራው ቅደም ተከተል ላይ በመመስረት አስፈላጊውን የመለኪያ መሳሪያዎችን በመምረጥና እና በመገጣጠም ስራዎን ያከናውናሉ። ከብየዳው በኋላም የስራውን ወጥነት ፤ ሽግግሮች ትክክለኛ መሆናቸውን፤ እና ስንጥቆች አለመኖራቸውን ያረጋግጣሉ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ??
- ቅልጥፍና እና የእጅ ዓይን ቅንጅት (ለምሳሌ የመገጣጠሚያ ነጥቦቹን በትክክል ሲያስተካክሉ)
- እንክብካቤ (ለምሳሌ ክፍሎችን ሲያጸዱ እና ሲጠግኑ)
- የኃላፊነት ስሜት (ለምሳሌ ሲፈትሹ)
- ጥንቃቄ (አካባቢን እና እራስዎን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ).
- የቦታ ምናብ (ለምሳሌ በቴክኒካዊ ስዕሎች መሰረት የብረት ግንባታዎችን ሲገጣጥሙ)
ሊወዷችው የሚችሉ ሌሎች ዘርፎች
የሴራሚክ ባለሞያ
ይህ ሙያ የሚያጠነጥነው የተለያዩ ንጣፎች በመስራት ላይ ነው።
የጡብ ባለሞያ
ይህ ስራ ለመኖሪያ እና ለንግድ ቤት ግንባታ የሚሆኑ ጡቦችን የማዋዋቀር እና ማምረት ስራ ነው።
ቀለም ቀቢ
ይህ የሙያ ዘርፍ ቀለም መቀባትና ተያያዥ ስራዎችን ያካትታል።
አናጢ
ይህ የስራ ዘርፍ እንጨት እና ከእንጨት ስራ ጋር ተያያዥ ስራዎችን ያክትታል።